
Parenting training for mothers
The original post, as shared on Telegram
ረጃጅም ህንጻዎች ትናንሽ ትእግስቶች ፤ ሰፋፊ መንገዶች ጠባብ አመለካከቶች፤ የምናወጣው ብዙ የሚኖረን ጥቂት፤ ብዙ እንገዛለን ትንሽ እንደሰታለን፡፡
ትላልቅ ቤቶች ትናንሽ ቤተሰቦች፤ የተሻለ ምቾት ጥቂት ጊዜ፤ ብዙ ድግሪ ትንሽ ማመዛዘን (ግንዛቤ)፤ ብዙ እውቀት ትንሽ ጥበብ ፤ ብዙ አዋቂዎች ብዙ ችግሮች ፤ ብዙ መድሃኒት ትንሽ ጤንነት ፡፡
ስለ ጥሩ አኗኗር ተምረናል እንዴት እንዴት እንደሚኖር ግን አልተማርንም ፡፡….ለህይወት እድሜ ጨምረንለታል ለእድሜ ግን ህይወት አልጨመርንም፡፡
ስልጣንን ለማገልገል ሳይሆን ሆድ ለመሙላት ፤ ሆድ ተንዘርጥጦ አምሮ ግን ኮሰመነ፡፡ ጨረቃ ላይ ደርሰን ተመለስን ግድግዳ የሚለየውን አዲስ ጎረቤታችንን መተዋወቅ አቀበት ሆነብን፡፡ ከምድራችን ውጪ ያለውን ህዋ ተቆጣጠርን ፡፡ በውስጣችን የሚገኘውን ትንሽ ቦታ ግን አልተቆጣጠርንም፡፡
ትላልቅ ነገሮቸን እንጂ የተሻሻሉ ነገሮችን አልሰራንም ፡፡ አካባቢያችንን እያጸዳን ነፍሳችንን ግን እየበከልን ነው ፤ አቶምን ሰነጠቅን መሰረተ-ቢስ ጥላቻዎቻችንንና ቅራኔዎቻችንን ግን አልፈታንም ፡፡
ብዙ እናነባለን ትንሽ እንለወጣለን ፤ ብዙ እናቅዳለን ጥቂት እናሳካለን፡፡ መቸኮልን እንጂ መጠበቅን አልተማርንም ፤ የተሻለ ገቢ እንጂ ያደገ ስነ-ምግባር የለንም፡፡
ብዙ መረጃ የሚይዝና ብዙ ሥራ ባጭር ጊዜ የሚያከናውን ኮምፑዩተር ፈጠርን እንጂ በመካከላችን ግን ብዙ መግባባት አልተፈጠረም ፤ በብዛት ብዙ ሄደናል በጥራት ግን ወደ ኃላ ተጎትተናል፡፡
ጊዜው እንዲህ ሆነ፡- ሰው በሁለት ገቢ የሚተዳደርበት ትዳር ግን የሚበተንበት ፤ የተሰነጣጠቁ ቤተሰቦች የሚኖሩባቸው ግን የተዋቡ መኖሪያዎች ፡፡ ወቅቱ ፈጣን ጉዞ የሚደረግበት፤ ለአንድ ሌሊት ትዳር የሚወጣበትና ግብረ -ገብነት ተሽቀንጥሮ የተጣለበት ዘመን።
በዶ/ር ተስፋዬ ሰለሞን Parenting training: look at this beautiful and hero moms who are committed to raise their children and still want to know more and learn more!
Photographs 3
In context
How this post fits into the record of our work since 2020.





